በድሬደዋ አስተዳደር ከትምህርት ቤቶች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ክበባት አስተባባሪ መምህራን እንዲሁም በፈጠራ ላይ የሚሰሩ ተቋማት ተወካዮች የተሳተፉበት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡ በዚህ መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ሀላፊ የሆኑት አቶ ፉኣድ ሱጌ በሀገራችን የልማት ጉዞ የኢኖቬሽን ዘርፍ የበኩሉን ሚና እንዲያበረክት በየጊዜዉ አቅሙን መገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
በድሬደዋ አስተዳደር የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሀሩን አብዱራህማን በበኩላቸዉ ትምህርት ቤቶች ለሳይንስ ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መሰረት በመሆናቸው ሀገራችን በኢኖቬሽን ዘርፍ የያዘችዉን አላማ ለማሳካት ብሎም ህብረተሰባችንን የኢኖቬሽን ውጤቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ለዘርፉ መሰረት ለሆነዉ የትምህርት ቤት ክበባት አስተባባሪዎችን አቅም ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የሳይንስ ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ለዓለም ስልጣኔ ያበረከተዉ ድርሻ እንዲሁም የዓለም ሀገራት ዕድገት ከሳይንስ ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ጋር ያለዉን ትስስር የሚያሳይ ፁሁፍ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡


