የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የ6 ወር የስራ አፈፃፀሙ ላይ ከተቋሙ ባለሙያዎች ጋር ዉይይት አደረገ::

    የአስተዳደሩ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰራተኞች በተቋሙ የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ዙሪያ ዉይይት አካሄደዋል ፡፡
    ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት የላቀ ውጤት ካስመዘገበባቸው ዋንኛዎቹ በሪፖርቱ ከተጠቀሱት የለውጥ ስራውን ተግባራዊ ማድረግ፣ የኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ባለሞያዎችን የሞያ አቅም ግንባታ ስራና ቢሮው በዚህ ግማሽ ዓመት የስራ ቦታን ምቹ እና የተዋበ በማድረግ የሰራተኛውንና የተገልጋዩን እርካታ ለመጨመር ሲያከናዉናቸዉ የቆያቸውን ስራዎች መሆናቸውን በመድረኩ ለባለሙያዎች ቀርቧል፡፡
    በመድረኩ የተሳተፉ የተቋሙ ባለሙያዎች በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጣይ የታዩ ክፍተቶችን እና ያልተከናወኑ ተግባራትን ውጤት ለማስመዝገብ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡
    በመድረኩ ላይ ለተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የቢሮው ኃላፊ አቶ እስቂያስ ታፈሰ ማብራሪያ በመስጠትና የቀጣይ ስድስት ወራት የስራ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡