ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ማህበረሰብ ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑ ተገለፀ።

    በአገሪቱ ያለውን የጤና ፋይናንስ ክፍተት ለመሙላት ከጥቂት ዓመታት በፊት በመንግሥት ይፋ የተደረጉት የጤና መድኅን አይነቶች ሁለት ናቸው፡፡
    ማኅበራዊ የጤና መድኅን በመደበኛው ክፍለ ኢኮኖሚ የተሰማራውን፤ ማኅበረሰብ አቀፍ ደግሞ ደመወዝተኛ ያልሆነውንና መደበኛ ባልሆነው ክፍለ ኢኮኖሚው የሚገኘውን ያቀፈ ሲሆን በድሬደዋ አስተዳደር በታህሳስ ወር ጀምሮ ማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት (ደመወዝተኛ ያልሆኑትን)ማህበረሰቦችን አገልግሎት መስጠት ቢጀመርም አፈፃፀሙ ዝቅተኛ በመሆኑን የገለፁት የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና መድህን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ አበበ ገልፀዋል።
    ሥራ አስኪያጁ ከዚህም ጋር አያይዘው ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ለማግኘት ምዝገባው የሚቆየው እስከ የካቲት 30/2013ዓ ዓ.ም በመሆኑ ማህበረሰቡ ቀበሌ በመሄድ መመዝገብ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
    የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፉ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በውይይቱ ላይ ለህብረተሰቡ ባስተላለፍት መልዕክት ማህበረሰቡ በጤና መድህን በመሳተፍ የጤና አገልግሎት የማግኘት መብታቸውን ማጎልበት ይኖርባቸዋል በማለት የጤና መድህን ተጠቃሚ ማህበረሰቦች የጤና አገልግሎት ለማግኘት ከጤና ጣቢያ ሪፈር ሳይባሉ ወደ ድል ጮራ ሆስፖታል ከሄዱ የአገልግሎቱን ግማሽ ክፍያ እንደሚከፍሉ ጠቁመዋል።
    የድሬዳዋ ብልጽግና ፖርቲ የህዝብ ግንኙነትና ሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዶ አሊ ባወያዩበት ወቅት እንደተናገሩት የዛሬው ተሳታፊዋች ከዛሬ ጀምሮ የቅስቀሳ ስራ፣ ማህበረሰቡን የማወያየትና ባሉን የሚዲያ አውታሮች ሁሉ ተጠቅመን ማህበረሰቡ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት ይኖርብናል ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
    በውይይቱ የተሳተፍ ባለድርሻ አካላትም በሰጡት አስተያየት ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ በቅንጅት በመስራት ያሉ ክፍተቶችን በመፈተሽ ህብረተሰቡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የድርሻውን መዉጣት ይጠበቅበታል በማለት የተጣለባቸውን ኃላፉነት ለመወጣት እንደሚሠሩም ገልፀዋል።
    በዛሬው እለት የድሬዳዋ ጤና መድህን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ የሚዲያ፣ የቀበሌ ኮሙዪኒኬሽን ኃላፉዋችና የእድር ሰብሳቢዋች ተገኝተዋል።