125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በድሬደዋ ከተማ ተከበረ፡፡

    125ኛው የዓድዋ ድል በዓል ድሬደዋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
    በዓሉ በድሬደዋ አስተዳደር “ዓድዋ የኅብረ ብሔራዊ አንድነት አርማ!” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል።
    በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እንደተናገሩት የአድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካዋያን የነፃነት ብርሀን የፈነጠቀ ነው ብለዋል፡፡
    ምክትል ከንቲባው አክለውም የ125ኛው የአድዋ ድል በዓል ስናከብር ጀግኖች አርበኞች ለዋሉልን ውለታ ምስጋና አክብሮት ከመቸር ባለፈ በብዙ ድካምና ዋጋ ያቆዩልንን ሀገራችን ህብረ ብሔራዊ ማንነታችን በመጠበቅና የብልጽግና መንገዳችንን ከግብ በማድረስ የድርሻችንን መወጣት አለብን ብለዋል፡፡
    የአድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ተርፎ ለአፍሪካና ለዓለም ጥቁር ህዝቦች መመኪያና መኩሪያ የሆነ ታላቅ ድል እንደሆነ የተናገሩት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙራድ በደዊ ይህ ታላቅ ድል ለ125ኛ ጊዜ ስናከብርና ስንዘክር የጦርነቱን መንስኤዎች፤ የኢትዮጵያውያንን የዲፕሎማሲ ትግል እና ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ለነፃነት የከፈሉትን መስዋዕትነት በማሰብ ልናከብረው ይገባል ብለዋል፡፡
    በመረሐ-ግብሩ ላይ የድሬደዋ ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት አባላት እና አመራርች እንዲሁም የአስተዳደሩ ነዋሪዋች ታድመዋል።