በክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተነደፉ በርካታ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የሀገራችንን የንግድ አሰራር የማቀላጠፍና አሁን ካለበት ዝቅተኛ ደረጃ የአለም ባንክ በየአመቱ የሚያወጣውን የሀገራት ደረጃ የሚያሟላ ተደርጎ የተቀረፀው ሀገራዊ ፕሮጀክት እቅድ ላይ በዛሬው እለት በድሬዳዋ አስተዳደር የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ኢኮቴ) እና ከንቲባው ፅ/ቤት ሳይንስና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ በሚመለከታቸው በአስተዳደራችን ውስጥ ያሉ ከፍተኛ የዘርፉ ባለሞያዎችን በማካተት ከኢፌድሪ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተውጣጡ ከፍተኛ ሀላፊዎችና ባለሞያዎች ጋር በፕሮጀክቱ አጠቃላይ ጠቀሜታ፣ አስፈላጊነት እንዲሁም ለተጠቃሚው የሚሰጠውን ጥቅም ዙሪያ ሠፊ ውይይትና መግባባት ላይ ለመድረስ ተችሏል።


