በድሬዳዋ አስተዳደር ለትግራይ ክልል ወገኖቻችን የሀብት ድጋፍ አሰባሰብ ስራው በይፋ ተጀመረ።

    በትግራይ ክልል ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችን ላይ በጁንታው የጥፋት ሀይል የደረሰውን ጥቃት በመመከት እና ህግ እና ሰርአት የማስከበሩ ተግባር መሰዋትነት ተከፍሎ በድል መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
    የህግ የማስከበሩ ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ የጁንታው ሐይል ያደረሰውን ውድመት ተከትሎ በአካባቢው የከፋ የሰብአዊ ጥፋት እንዳይከሰት ከፍተኛ እርብርብ ሲደረግ ቆይቷል። መንግስት የቻለውን ያህል ችግሩን ለመቀልበስ እየጣረ የሚገኝ ቢሆንም የጁንታው ርዝራዦች በየሚዲያው በሚያናፍሱት አሉባልታ ምክንያት አንዳንድ መንግስታት ሳይቀሩ መንግስት እያደረገ ያለውን ርብርብ ለማጣጣል ሲሞክሩ ተስተውለዋል፡፡
    በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖቻችንን ካጋጠማቸው ሰብዓዊ ቀውስ የፓርቲያችን መርህ እና እሴት ከምንም በላይ ሰብዓዊነትን (ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው) ስለሚያስቀድም ከዚህ ባሻገር ኢትዮጵያውን የምንታወቅበት ጠንካራ የመረዳዳትና የማካፈል ባህል አንጻር መታየት ይኖርበታል፡፡ ለወገን ደራሽ ወገን ስለሆንም ነው፡፡
    የድሬዳዋ አስተዳደርም 5 ሚሊየን ብር ከበጀቱ በመቀነስ ለዚሁ ተግባር እንዲውል የመደበ ሲሆን ድጋፉን በማጠናከርም ከተለያዩ የህብረተሰብ ከፍፍሎች ከባለሃቶች፣ በበጎ አድራጊ ግለሰቦች፣ አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች ተቋማት ወዘተ ሃብት ለማሳባሰብ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡
    በዚሁ መሰረት በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኞቻችን ያጋጠማቸውን ችግር ለመቅረፍ በገንዘብና በቁሳቁስ ሀብት በማሰባሰብ ለወገኖቻችን በችግራቸው ግዜ ደራሽ መሆናችንን ለማስመስከር በገንዘብ እና በቁሳቁስ መልክ ለመሰብሰብ በተለያየ የእርከን ደረጃዎች የሚገኙ የፓርቲና የካቢኔ አመራሮችና አባላትን ያቀፈ በአስተዳደር ደረጃ አንድ አብይ ኮሚቴና ሌሎች ንኡሳን ኮሚቴዎች የሚኖሩት አደረጃጀቶች እንቅስቃሴ ተጀምሯል።