ዩኒቨርሲቲው ከድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በመሆን በተለይም ህብረተሰቡ የውሃ አቅርቦትን የሚያገኙባቸውን መንገዶች ጥናት በማድረግ ማህበረሰቡ በአቅራቢያው ውሃ የሚያገኙበትን መንገድ ጥናት ለማካሄድ የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
በውሉ መሰረትም የቦኖ ውሃ በድሬዳዋ በተለምዶ ገንደ ተስፋ ለገኦዳ ሰፈር ይሰራሉ
በውል መፈራረሙ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዚዳንትና የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ለአስተዳደሩ ማህበረሰብ የሚሰጠውን እንደዚህ ዓይነቶቹን የምርምር አግግሎቶችን በማስፋትን ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናቶች ከአስተዳደሩ ጋር በመተባበር ያከናውናል ብለዋል፡፡
የአስተዳደሩ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን ወክለው የስምምነት ውሉን የፈረሙት አቶ ደረጀ ኩርቱ ዩኒቨርሲቲው በዚህ የምርምር ውል መሰረት 3 የውሃ ቦኖና የመስመር ዝርጋታ ያካተተ ነው ብለዋል፡፡


