የፕሮጀክቱ የቤዝ ላይንና የዲዛይን ጥናት ለድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የማስተዋወቂያ መድረክ በሐረር ከተማ ራስ ሆቴል ተካሂዷል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪኃጅ ፅ/ቤት UIIDP /የከተማ የተቀናጀ ተቋማዊ ልማት ፕሮግራም/
ስድስት ሚሊየን ብር በሚጠጋ ድጋፍ በሐሮማያ ዩንቨርሲቲ እየተደረገ የሚገኝው ጥናቱ የአስተዳደሩን የቀጣይ መቶና ሁለት መቶ አመታት ሁኔታ ትንበያ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ በመስተዋወቂያ መድረኩ ተገልጿል።
በቀረበው የጥናቱ ደረጃ ላይ በርካታ ሐሳብ አስተያየቶች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ፕሮጀክቱ የከተማዋን ልማት ከማፋጠን አኳያ የሚኖረው ፋይዳ እጅጉን የጓላ እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል።ከውይይቱ የተገኙ ሀሳቦችን እንደ ግበአት በመውሰድ ቀጣይ የፕሮጀክቱ ጥናት በተቀመጠለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ተገልጿል።


