ማህበረሰቡ በመንገድ ለውጡ ላይ ያነሳውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የአስተዳደሩ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሳ ጣሀ ፤የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ፤ በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ ፤ እንደሁም በድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢኒስፔክተር ይሄነው ሽፈራው ጨምሮ ሌሎች ሚመለከታቸው ባለድርሻዎች በስፍራው ተገኝተው የመንገድ ፍሰቱን ተመልክተዋል፡፡
ከምልከታው በኋላም የሚከተለው የመንገድ ማሻሻያ እንዲደረግ መወሰኑን በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ጉልማ ታዬ የሚከተለው ማሻሻያ እንዲደረግ መወሰኑን ገልፀዋል፡፡
በተለዋጭ መንገዱ ላይ የተደረጉየማስተካከያ እርምጃዎች….
ሰኢዶ መስቀለኛ ላይ የትራፊክ መብራት ግንባታውን በአጭር ግዜ ውስጥ ለማከናወንና ትራፊክ መብራቱ ስራ መጀመርንም ተከትሎ የተሸከርካሪ ፍሰቱም መቀነስ ስለሚገባ ከሼል፣አሸዋ፣ኮኔል የሚነሱ ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በሳቢያን እግር ኳስ ሜዳ ጀርባ የሚያልፈውን ኮብል ስቶን መንገድ ተጠቅመው መዳረሻቸውን ቄራ እንዲያደርጉና ዞረው ሲመለሱ በሰኢዶ በሚያልፈው ዋና መንገድ ተሳፋሪ እያነሱ እንዲሄዱ በከተማ አስተዳደሩ የመንገድ ጉዳይ የሚመለከታቸው ተቋማት ባደረጉት የጋራ ስምምነት ውሳኔ ተላልፎ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ይሁንና በውሳኔው የተደረገው የመንገድ ለውጥ በዋናው ሰኢዶ መስመር መንገዱ ላይ የትራፊክ መጨናነቁን በመቀነስ ጤናማ ፍሰት እንዲኖርና የትራፊክ መብራት ተከላ ስራውን ለማከነውን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ተለዋጭ መንገዱንና ቄራ ታክሲ ፌርማታውን በተመለከተ መልሶ ማየት
በማስፈለጉ፡- ከእነዚህ የተለያዩ ስፍራዎች ተሳፋሪ ይዘው በተለዋጭ መንገዱ ወደ ሳቢያን የሚመጡ ታክሲ ተሸከርካሪዎች ተሳፋሪዎችን በተለያዩ ቦታዎች አውርደው ከጨረሱና ባዶ ከሆኑ ባዶአቸውን ቄራ ሄዶ ዞሮ መምጣትን ለማስቀረት መንገድ አጠቃቀሙ ላይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈልጓል፡፡
በዚሁ መሰረት የትራፊክ መብራት ተከላ ስራው ሂደት እንዳለ ሆኖ፡- ከ25/7/2013ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ግዜ
1- በተለዋጭ መንገዱ የሚመጡ ታክሲዎች ብሔራዊ ሆቴልን አልፈው ወደ ግራ ወደ ሰኢዶ በመታጠፍ መስቀለኛውን ሳይሻገሩ ቆመው የትራፊክ ህግን ባከበረ ሁኔታ ወደ ሼል፣አሸዋ፣ኮኔል ተሳፋሪ እንዲጭኑ ተፈቅዷል፡፡
2- የታክሲዎች ስፍራውን መጠቀምን ተከትሎ መጨናነቅ የሚፈጠርና አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ
2.1- ለግዜው ከሰኢዶ መስቀለኛ ወደ ቀኝ ወደ እሸት መንገድ መታጠፍ የማይቻልና ዝግ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ሌላ አማራጭ መንገድ መጠቀም እንዲችሉ
2.2- ሰኢዶ መስቀለኛ የደረሰ ማንኛውም ተሸከርካሪ ወደ ግራ ታጥፎ ወደኋላ ዞሮ መመለስ/ U-TURN የማይቻል መሆኑን እየገለፅን ፤ ትራፊክ መብራቱ ተተክሎ ሙሉ በሙሉ ስራውን እስኪጀምርና የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት አስኪፈጠር አሽከርካሪዎችም ሆኑ ሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች በትዕግስትና በመቻቻል መንፈስ መንገዱን እንድንጠቀሙ እናሳስባለን፡፡
ምክትል ኮማንደር ጉልማ ታዬ
በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንገድ ትራፊክ ደህንነትማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ምንጭ :-የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፌስቡክ ገጽ


