1442 ተኛውን ታላቁን የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከሰራተኞቹ ጋር በጋራ የአፍጢር ፕሮግራም አካሂዷል ።

    ታላቁ የረመዳን ፆም በድሬዳዋ አስተዳደር በጋራ ከማፍጠር ባለፈ ያለው የሌለውን በመርዳትና በመደጋገፍ ፆሙን እያሳለፍ ይገኛሉ ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ፆሙን ምክንያት በማድረግ ከቢሮው ሰራተኞች ጋር በጋራ የማፍጠር ስነ-ስርአት አካሂዷል።
    በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ እስቂያስ ታፈሰ የረመዳን ፆም በከተማችን ድሬዳዋ ላይ ሲከበር በተለይም በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ አንድነትን ፣ መተሰባሰብን ፣ መደጋገፍን እንዲሁም መረዳዳትን ከመፍጠሩም ባለፈ ፆሙን ምክንያት በማድረግ ከሰራተኞቹ ጋር በጋራ በማፍጠር ለሙስሊም ወንድም እህቶች ለሆኑ የቢሮው ሰራተኞች ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጎልበት ትልቅ አጋጣሚን የሚፈጥር ፕሮግራሙ መሆኑን አቶ እስቂያስ ታፈሰ ተናግረዋል ።
    በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ውስጥ ከሚሰሩ ሰራተኞች ጋር በጋራ ማፍጠሩ በተለይም ከተማችን ድሬዳዋ የምትታወቅበትን በጋራ ተቻችሎ የመኖር እሴትን ከማጠናከር ባለፈ ቢሮውም በሰራተኞች መካከል ቤተሰባዊነትን ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከርና በመጠበቅ ደረጃ አስተዋፆው የጎላ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ አካላትን ማብቃትና ማፍራት ዳይሬክተር ሚካኤል እንዳለ ተናግረዋል ።
    1442 ተኛው ታላቁ የረመዳን ፆም ወንድማማችነትን አብሮነትን መደጋገፍን በይበልጥ የሚያጎላ እንደመሆኑ መጠን በቢሮው አዲስ ከተቀጠሩ ሰራተኞች ጋር በጋራ ማፍጠሩ ከሰራተኞቹ ጋር በይበልጥ ለመተዋወቅም ጥሩ አጋጣሚን እንደሚፈጥር የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሚልኬይሳ ሙሜ ተናግረዋል ።
    በፕሮግራሙ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የቢሮው ሰራተኞች በበኩላቸው የእምነቱ ተከታይ ለሆኑ ሰራተኞች በጋራ የአፍጢር ፕሮግራም በማዘጋጀቱ መደሰታቸውንም ተናግረዋል ።