በመድረኩ ዘጠኝ ፖርቲዎች የተሳተፈ ሲሆን የጋራ መግባቢያ የቃል ኪዳን ሰነድ ተፈራርመዋል።
የፖለቲካ ፖርቲዎች መካከል የጋራ መድረክ መመስረቱ:-
*በተፎካካሪ ፖርቲዎች መካከል በመተማመን ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ውይይት እንዲኖ ለማስቻል ።
*በመደማመጥና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ምክንያታዊ ውይይት እንዲኖር።
*የአገራዊ ጥቅምን ቅድሚያ መስጠትን።
*የህዝብን ጥቅም ማስቀደም።
*መሰረታዊ የሆኑ የሰብዓዊና የእኩልነት መርሆዎችን የተከተለ የጋራ የምክክር መድረክ በዘላቂነት እንዲኖር ለማስቻል ።
*በቀጣይ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ።
***የፖለቲካ ፖርቲዎች የሚዲያ አጠቃቀምን ህግንና ስርአትን የተከተለ ለማድረግ ።
ባጠቃላይ ምርጫና ምርጫ ነክ የሆኑ ጉዳዬችን በሰላማዊ መንገድ ለማከናወን የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ መድረኩ መመስረቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በምስረታና የቃል ኪዳን ሰነድ መፈራረሚያ ስነስርአቱ ላይ ተገልጿል።


