የመራጮች ምዝገባ ከአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ውጭ ዛሬ በሚጠናቀቅባቸው ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የመራጮች ምዝገባ እስከ አርብ ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ለተጨማሪ 07 ቀናት እንዲከናወን መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ቦርድ እንዳስታወቀው በመጀመሪያ ሰሞን የነበረው የመራጮች ምዝገባ እየተሻሻለ መሆኑ እና ተደራራቢ የበዓል ቀናት ዝግ በመሆኑ ምርጫ ካርድ መውሰድ ሲገባቸው ያልወሰዱ ዜጎች መኖራውን ከግምት በማስገባት ቀኑ እንደተራዘመ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ዛሬ የመራጮች ምዝገባ ይጠናቀቅባቸው በነበሩ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በኦሮሚያ ክልል በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ በጋምቤላ ክልል፣ በሃረሪ ክልል፣ እና በሲዳማ ክልል የመራጮች ምዝገባ ለ7 ቀናት እንዲራዘም ተደርጓል ብሏል ቦርዱ፡፡
በዚህ መሰረት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት እስከ ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የመራጮች ምዝገባ እንደሚከናወን ቦርዱ ገልጿል።
ያለፉትን ሶስት ቀናት ሳይጨምር በ41 ሺህ 798 የምርጫ ጣቢያዎች 28 ሚሊዮን 7 መቶ 31 ሺህ 935 ዜጎች በመራጭነት እንደተመዘገቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡
ምንጭ፦EBC


