የ 9 ወራት የስራ አፈፃፀም በተመለከተ የመስክ ምልከታ ተካሄደ ::

    በድሬ ደዋ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማናጅመንት አባላትና ባለድርሻ አካላት በጽ/ቤቱ የሚገኙ ተቋማት እየተካሄዱ የሚገኙ ፕሮጄክቶች የ 9 ወራት የአፈፃፀም ግምገማ ከሪፖርቱ ባሻገር በተጨባጭ ፕሮጄክቶቹ ያሉበትን ደረጃ በመዘዋወር የጎበኙ ሲሆን በፕሮጄክቶቹ በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ የሚገቡ ስራዎች ፣ መሻሻል ያለባቸዉ ተግባራትና ፕሮጄክቶቹ ከዕቅድ አንፃር ያሉበትን ደረጃ ጎብኝተዋል ፡፡
    በዚህ ጉብኝት ከተጎበኙ ፕሮጄክቶች መካከል የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ፓርክ የአጥር ግንባታ፣ የድሬ ደዋ የመጠጥ ዉሃ ማሻሻያ ፕሮጄክት ፣ የሃፍካት ድልድይ እንዲሁም የዉስጥ ለውስጥ መንገዶች የድንጋይ ንጣፍ ስራ ከተጎበኙ ፕሮጄክቶች መካከል ናቸዉ፡፡
    የድሬ ደዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልጀዋድ መሀመድ በዚህ ጉብኝት ላይ ከምንም በላይ ለስራዎቹ ጥራት ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባና እነኝህ ፕሮጄክቶች በተያዘላቸዉ ጊዜ ተጠናቀዉ ለህዝቡ አገልግሎት መዋል እንዲችሉ ተቀናጅተዉ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡