በድሬዳዋ አስተዳደር የአፍጢር ፕሮግራም በድምቀት ተካሄደ፡፡

    በዚሁ ዝግጅት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ እና የተለያዩ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተካሄደው የአፍጢር ፕሮግራም ላይ በርካታ ህዝበ -ሙስሊሙ ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡
    ድሬዳዋ ከተማ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እና የተለያዩ እምነት ያላቸው ነዋሪዎች በፍቅር እና በአንድነት የሚኖርባት ነው ያሉት ም/ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ይሄን የአብሮነት እና የፍቅር ተግባር በሚያስቀጥል መልኩ ይሄ የአፍጢር እና የአንድነት ዝግጅት መደረጉ ትልቅ ዋጋ አለው ብለዋል፡፡
    ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው ድሬዳዋ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላም የሰፈነባት ከተማ መሆኗን ጠቅሰው ይሄ የአፍጢር ፕሮግራም መዘጋጀቱ አይነተኛ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
    በዚህ የአፍጢር ፕሮግራም ላይ የአድማ እና ልዩ ሁነት ጥበቃ ዲቪዥን እና የድንገተኛ እና እሳት አደጋ አመራር እና አባላት የአፍጢር ፕሮግራም የተካሄደበትን ቦታ ከሰፈር አንድ እስከ ገንደ -ገበሬ ያለውን የአስፋልት መንገድ ለአፍጢር ፕሮግራም ምቹ ለማድረግ ፅዳት ያከናወኑ ሲሆን የለገሃሬ ቀበሌ እና የአካባቢው ወጣቶች ዝግጅቱን በማስተባበር ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡
    ምንጭ፡ ድሬ ፖሊስ