መረጃ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ…..

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር ይታወቃል። በየምርጫ ጣቢያዎቹ የሚደገረው መራጮች ምዝገባ ቢጠናቀቅም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ መሰጠት እንዳለበት ቦርዱ ወስኗል። በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ድረስ https://www.ovrs.gov.et በሚገኘው የመመዝገቢያ ሊንክ በመጠቀም እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
    የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምዝገባ ሊንክ ድረ-ገጻችን www.nebe.org.et ላይም ይገኛል።
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ