አገራችን የገጠማትን ወቅታዊ ውጫዊና ውስጣዊ ችግሮች በተባበረ መንገድ በመፍታት ወደ ብልጽግና የሚደረገው ጉዞ እንዲሳካ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን እንዲወጣ የብልጽግና አመራርና አባላት ጠየቁ ፡፡

    የድሬዳዋ አስተዳደር የብልጽግና አመራርና አባላት ዛሬ በምድር ባቡር አደባባይ በማስ ስፖርት የምረጡኝ ቅስቀሳ አድርገዋል ፡፡
    በምረጡኝ ቅስቀሳው መልዕክት ያስተላለፉት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሐር በድሬዳዋ መለያ በሆነው ወንድማመችንት የታመመውን በማሳከም ፤ የታረዘውን በማልበስ ፣ የተቸገረን በመርዳትና በህብረት በመቆም ወደ ብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ እንዲሳካ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
    በወጣቶችና ስፖርት የለውጥ ስራና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ስላማዊት ግርማ ሀገራችን ያለችበትን ችግር ለመፍታት የአንድ ፓርቲ ኃላፊነት ብቻ አይደለም ፤ ሁሉም ዜጋና ፓርቲ የሀገራችንን ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ ለዩነትን አስወግደን በጋራ በመቆም ብቻ ነው ብለዋል ፡፡
    በማስ ስፖረቱ ላይ የተገኙ በርካታ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና ደጋፊዎች የተናገረውን የሚፈጽመውን የሚበራ አምፑል ምልክቱ የሆነውን ብልጽግናን ፓርቲ ምረጡ በማለት የቅስቀሳ ዘመቻቸውን አከናውነዋል ፡፡