የግብርና ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የስርአተ ምግብ ተጠሪ ወ/ሮ ሽልማት እንግዳ የስልጠናውን አስፈላጊነት አስመልተው በተናገሩት ንግግር በ2030 ዓ.ም እንደ ሀገር ብሎም በአስተዳደራችን ከተቀመጠው አንዱና ዋና አላማ በህጻናት መቀንጨር ለመግታት ሲሆን ግንዛቤ መፍጠር ማዳበር ሂደት አንዱና ዋንኛው መሆኑን በመግለፅ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ በመፍጠር ሂደት በተለይም በገጠሩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ነዋሪዎችን ግንዛቤ ለመፍጠር የስልጠናው ተሳታፊዎች የድርሻችሁን መወጣት ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡
ከዚህም ጋር አያይዘው ወ/ሮ ሽልማት የተመጣጠነ ምግብ ምንነት እንዲሁም አስፈላጊነቱን ለማህበረሰቡ ለማስገንዘብ የልማት ጣቢያ ሰራተኞች ሰፊ ሚና አላችሁ በማለት የጋራ እርብርብ በማድረግ በአካልም ሆነ በአዕምሮ የዳበረ ዜጋ ማምረት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ቀደም ብሎ የምናከናውናቸው ተግባራት ቢሆኑም ስልጠናው ገና የሚቀረን ስራ እንዳለን ያሳየን ነው በማለት በቀጣይ ማህበረሰቡ በየጎራቸው አትክልቶችን እንዲያመርቱ እና እንዲመገቡ የማድረግ ስራ አጠናክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና
ሰልጣኞች የሰለጠኑት ስልጠና የተግባር ስራዎችም በመስራት ተጠናቋል።


