ከቀናት በኋላ በሀገራችን የሚካሄደውን 6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ ሲያካሂድ ቆይቷል ። የዚሁ የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ-ግብር አካል የሆነ ፕሮግራም በቀበሌ 02 ሳቢያን ኳስ ሜዳ ውስጥ የብልጽግና ፖርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ሻይ ቡና ፕሮግራም ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ መብራቴ ገብረየስ ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጲያዊያንና የብሄር-ብሄረሰቦች ፓርቲ ከመሆኑም ባለፈ ሀገራችን ኢትዮጲያን ወደ ተሻለ ከፍታ ለማበልፀግ ራእይ ያለው ፓርቲ እንደሆነ ተናግረው ህዝቦች በነፃነት ወተው የሚወክላቸውን የሚመርጡበት ስርአት ያመቻቸ ፓርቲ መሆኑን አቶ መብራቴ ገብረየስ ተናግረዋል ።
ቀበሌ 02 ትን ብሎም ከተማችን ድሬዳዋን የበለፀገች ሀገር ትሆን ዘንድ ነዋሪዎች ከመንግስት ጎን ከመቆም ባለፈ የነበረንን ህብረ-ብሄራዊነት ወንድማማችነት መቻቻልን ማምጣት እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር ተናግረው ብልፅግና ፓርቲ ሰላም እያረጋገጠ ሀገርን በመምራት ከህዝብ የተጣለባቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡም አቶ ከድር ተናግረዋል ።
ብልፅግና ፓርቲ በሚቀጥሉት 10 አመታት ሀገራችን ኢትዮጲያን በኢኮኖሚያቸው ብሎም በሀይል ሚዛናቸው ከጎለበቱ አምስት የአፍሪካ ታላላቅ ሀገራት ተርታ በማድረስ ሀገራችንና ህዝቦችን ወደ ብልፅግና የማሻገር ትልቅ ራእይ እንዳለው የ 02 ቀበሌ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ወንድማገኝ በሻህ ተናግረዋል ።
በመድረኩ ላይም በቀበሌው በእጩነት የቀረቡ የፓርቲው አባላትን የትውውቅና የምርጡኝ ቅስቀሳ ፕሮግራም ከመከናወኑም ባለፈ ስለፓርቲው የተለያዩ መልዕክቶች በደጋፊ አመራሮችና እጩዎች ተላልፏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በ 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የወጣቶችና የሴት ሚና በሚል መሪ ቃል በቀበሌ 03 ብልፅግና ፓርቲ አዘጋጅነት የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም በሳሚ መናፈሻ ሆቴል ተካሂዷል።
በዚሁ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም ብሄር ብሄር ብሄረሰቦች ብሎም በተለያዩ እድሜ ያሉትን ምንም አይነት ልዩነት ሳያሳይ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሰራ አቃፊ ፓርቲ መሆኑን ተናግረው ነዋሪዎችም ከብልፅግና ፓርቲ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባም አቶ አህመድ ተናግረዋል ።


