መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ ፓለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖሊሲዎችን በማውጣትና በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን በተለይም በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ይታወቃል ። የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ላይ በተለይም መንግስት ለዘርፍ ትኩረት በመስጠት ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ።
በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር በመካከለኛና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ላይ ችግሮች ካሉ በመፍታት በዘርፍ ከተሰማሩ አካላት ጎን መሆናቸውንም አቶ ከድር ጁሀር በእለቱ ተናግረዋል ።
አነስተኛ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች የድሬዳዋን የኢንዱስትሪ ማእከልነት የሚያረጋግጡ ብቻ ሳይሆኑ ለአልሚዎችና ለነዋሪዎቿ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቁና ለሀገራችንም የኢኮኖሚ እድገት የላቀ አስተዋፆ የሚያበረክቱ መሆናቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ምክትል ቢሮ ሀላፊና የአነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዲ ሙክታር ተናግረው በኢንዱስትሪ መንደር ከሚገኙት ኢንዱስትሪዎች በተጨማሪም አስተዳደሩ ባዘጋጀው ቦታ የተቋቋሙ በርካታ አምራች ድርጅቶች መኖራቸውንም አቶ አብዲ ተናግረዋል ።
በሞዴልነት የተመረጡ 21 ሞዴል ማኑፌክቸሪንግ ኢንደስትሪዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ከእለቱ የክብር እንግዳ ከመቀበላቸውም በዘለለ ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ 11 ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ 5 ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ በአጠቃላይ 16 ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የእድገት ደረጃ ሽግግርም አድርገዋል ።
በፕሮግራሙ ላይም የተለያዩ ቢሮ ሀላፊዎች ከመገኘታቸውም ባለፈ ከልማት ባንክ ፣ ከማይክሮ ፋይናንስ እንዲሁም ከቴክኒክና ሞያ እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።


