በአሰልሶ ገጠር የቀበሌ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ-ግብር አካሂዷል ።

    ከአራቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ገጠር ክላስተሮች አንዱ በሆነው የአሰልሶ ክላስተር በአሰልሶ ገጠር የቀበሌ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ-ግብር አካሂዷል ።
    በመርሀ-ግብሩ ላይ በመገኘት የድሬዳዋ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አልይ በዝግጅቱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ዕቅዶች እና ፕሮግራሞች በተልይም በት/ት እና የስራ ዕድል ፈጥራ ዘርፍ ፣ በማህበራዊ ዘርፍ፣ በገጠር ልማትና ግብርናው ዘርፍ እንዲሁም ለሴቶች እኩልነትና ተጠቃሚነት ብሎም ለሀገራችን እድገትና ብልፅግናን ዕውን ለማድርግ ቢመረጥ ለመስራት የያዛቸውን ዕቅድ አቅርበዋል።
    በሀገራችን ለሚካሄደው 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለአስተዳደሩ ም/ቤት እና አስተዳደሩን በመወከል ልህዝብ ተወካዬች ም/ቤት ፓርቲው ያቀረባቸው ዕጩዎች የማስተዋወቅ ስነ ስርዓትም ተካሂዷል።