በድሬዳዋ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በዛሬው እለት ተካሄደ ።

    በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የከተማና የገጠር ቀበሌዎች ላይ የሚኖሩ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በፕሮግራሙ ላይ የብልፅግና ፓርቲን የሚያወድሱ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ታድመዋል ።
    በእለቱም በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የአስተዳደሩ ከንቲባ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ኢትዮጲያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማላበስና የዲሞክራሲ ስርአትን ለመገንባት ላለፍት ሶስት አመታት በትጋትና በፅናት እየሰራ ተጉዞ በበርካታ ፈተናዎችና ውጣውረዶች ተፈትኖ በጥንካሬ እዚህ የደረሰ ፅኑ ፓርቲ መሆኑን ተናግረው ብልፅግና ፓርቲ ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ህብረ-ብሄራዊነት የፍትህ መጎናፀፊያ በመስጠት ሁላችንንም የምትመስል የበለፀገች ጠንካራ ፌደራላዊ ኢትዮጲያ ለመገንባት እየሰራ የሚገኝ በሁሉም ለሁሉም የሆነ ፓርቲ መሆኑን አቶ አህመድ ተናግረዋል ።
    የብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራሞች ሀገራችንን ከድህነት ፣ ህዝባችንን ከጉስቁልና ኑሮ እንዲሁም ወጣቶቻችንን ከስራ አጥነት ፣ ለማላቀቅ የሚያስችል ፕሮግራም ያለውና ለዚህም ተግባራዊነት በቁርጠኝነት የሚሰራና የሚተጋ ፓርቲ መሆኑን የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ መብራቴ ገብረየስ ተናግረዋል ።
    በድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎች በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ ባለፍት አመታት የነዋሪውን ፣ የወጣቶችን ብሎም የሴቶችን ተጠቃሚነትና እኩልነትን ከማረጋገጥ አኳያ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን መስራቱን ተናግረው በቀጣይም ብልፅግና ፓርቲ ለሀገራችን ልማትና እድገት የተሻለ ስራን እንዲሰራ ከፓርቲው ጎን እንደሚሆኑም ተናግረዋል ።