የብልፅግና ፖርቲ በቢዮ አዋሌ ክላስተር አዳዳ ቀበሌ ከነዋሪዎች ጋር የውይይትና የፕሮግራም ማስተዋወቂያ መድረክ አካሂዷል።

    በመድረኩ ፖርቲው በማህበራዊ ÷ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ በቀጣይ የሚያከናውናቸው እቅዶች ገለፃ የተደረገ ሲሆን በዋናነት ከነዋሪው የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሚንቀሳቀስ ተገልጿል።
    በፖርቲው ስር አዳዳ ቀበሌን ወክለው ለድሬደዋ ምክርቤት የሚወዳደሩ ሶስት እጩዎችን ማለትም:-
    * አቶ ኡመር እህመድ
    *ወ/ሮ ጫልቱ እህመድ
    *አቶ ከድር ኡስማን
    ለቀበሌው ነዋሪዎች አስተዋውቋል።
    በተመሳሳይ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ድሬዳዋን የሚወክሉ እጩዎችንም አስታውቋል።
    በቀበሌው ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸው ታውቋል።