የብልፅግና ፖርቲ ድሬደዋ አስተዳደር በቢዮ አዋሌ ክላስተር አዋሌ ቀበሌ ከነዋሪዎች ጋር የምረጡኝ ቀስቀሳ አካሂዷል።

    በቀስቀሳ ላይ ፖርቲው በማህበራዊ ÷ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ በቀጣይ የሚያከናውናቸው እቅዶች ገለፃ የተደረገ ሲሆን በዋናነት ከነዋሪው የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሚንቀሳቀስ ተገልጿል።
    በፖርቲው ስር አዋሌቀበሌን ወክለው ለድሬደዋ ምክርቤት የሚወዳደሩ ሶስት እጩዎችን ማለትም:-
    * አቶ ኑረዲን መሀመድ
    *ወ/ሮ ሳኒያ ሙስጠፋ
    *አቶ ሙራድ ሙክታር
    ለቀበሌው ነዋሪዎች አስተዋውቋል
    በተጨማሪ አቶ ኑረዲን መሀመድ እንዳሉት ፖርቲያችን ብልፅግናን ከመረጣቹ በቀበሌ ና በአስተዳደሩ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ጠንክረን እንሰራለን ቡለል ።
    በቀበሌው አራት ሺ ሁለት መቶ ሰላሳ ሁለት ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸው ታውቋል።