6 ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ ሰላማዊና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ ይካሄድ ዘንድ በድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ አቀፍ የሰላም ምክር ቤት ተቋቁሟል ይኸውም ምክር ቤት በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ በመመራት በ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የተወዳደሩ 10 የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የፌደራልና የአስተዳደሩ የፍትህና የፀጥታ ተቋማቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎችና ኡጋዞች ፣ የሲቪክ ማህበራት ፣ በአስተዳደሩ የሚገኙ የዘጠኙም ቀበሌ አመራሮች አባል ሲሆኑ ይህም የከተማ አቀፍ የሰላም ምክር ቤት በድሬዳዋ አስተዳደር የተካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ ፣ ሰላማዊና ፍትህሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጾኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል ።
የተለያዩ የውጪ ሀገራት ሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ ግፊት ቢያደርጉም ነገር ግን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ ለሀገራችን ኢትዮጲያ ትልቅ ድል መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ተናግረው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪም ምርጫው በጥሩ ሁኔታ እንዲሳካ እንዲሁም በሰላማዊ መንገድና በነፃ የሚፈልጉትንና የመረጡትን ፓርቲ የመረጠ በመሆኑ ለከተማው ነዋሪዎችም ክቡር ከንቲባው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅና ችግሮችም ካሉ በተቋቋም የከተማ አቀፍ የሰላም ምክር ቤት መሰረት ምርጫውን በስኬት ማጠናቀቅ እንደተቻለና ይሄም ስኬት እንደ ሀገር ብሎም እንደ አስተዳደር ሊጠናከሩና ሊበረታቱ እንደሚገባም የድሬዳዋ አስተዳደር የፍትህ ፀጥታና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሳ ጠሀ ተናግረዋል ።
በእውቅና ፕሮግራሙ ላይም የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የከተማው ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋፆ በምርጫው ላይ የተወዳደሩ 10 የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ምስጋቸውን በእለቱ ገልፀዋል፡፡
በዚሁም የምስጋና ፕሮግራም ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባን ጨምሮ በ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የተወዳደሩ 10 የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላቶችን፣ የፍትህ ፀጥታና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ፣ የፌደራልና የአስተዳደሩ የፀጥታ አካላት አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ አባገዳዎችና ሌሎች በአስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ አደረጃጀት አመራሮች በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል ።


