ድሬ ፖሊስ:-26-10-2013
በድሬደዋ ከተማ ቀበሌ 02 ሳቢያን መስቀለኛ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2013 አ.ም ከቀኑ ስድስት ገደማ በግንባታ ላይ በሚገኝ ህንፃ ሳቢያ ከሚገነባው ህንፃ ጎን ያሉ ሁለት የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችና አንድ መፀዳጃ ቤት በመፍረሱ በህንፃው ግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች ህይወት ያለፈ ሲሆን በአንድ ሌላ አብሮ በስራ ላይ የነበረ ግለስብም ላይም ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል::
አደጋው እንደ ደረሰ ከአካባቢው ህ/ብ እና ወጣቶች ጋር የፖሊስ ሀይሉ ከፍተኛ የነፍስ አድን ስራ ቢሰራም ሁለቱም ግለሰቦች በከፍተኛ ሁኔታ ፍርስራሽና አፈር ሸፍኗቸው የነበረ በመሆኑ ህይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን የገለፀው ፖሊስ አንድ ሌላ የአደጋው ተገጂ በአሁኑ ወቅት በህክምና መስጫ የጤና ክትትል እየተደረገለት እንደሆነና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝም ገልፃል::
ፖሊስ ጨምሮ እንዳስታወቀው በደረሰው በእዚሁ አደጋ ሳቢያ ሁለት መቶ ሀምሳ ሺ ብር የሚገመት ንብረት እንደወደመ ገልፆ ከተከሰተው አደጋ ጋር ተያይዞ እየተገነባ ያለው ህንፃ ባለቤት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሆነም አስታውቋል::
የድሬደዋ ፖሊስ በሟቾች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘንም ገልፆ ለመላው ቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ መፅናናትን ተመኝቷል::


