በድሬዳዋ አስተዳደር አራቱንም ክላስተሮች ባሳተፈው እና 16 ቀበሌዎች የተሳተፉበት ስልጠና ተካሄደ፡፡160 ሞዴል ሴቶችን በስርዓተ ምግብ ዙሪያ ላለፉት አራት ቀናት ግንዘቤ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
የምግብ እና ስራዓተ ምግብ ስልጠናው ለሞዴል እማወራዎች የተሰጠው በስራዓተ ምግብ ረገድ የሚስተዋለውን ሰፊ ችግር ባገናዘበ መልኩ ነበር፡፡የህፃናት በምግብ እጥረት መጎዳት፣በተመጣጠነ ምግብ አጠቃቀም ስርዓተ አለማወቅ ልዩ ልዩ በሽታዎች መከሰት፣በእናቶች እና መላው ሴቶች ላይ የሚከሰቱ የጤና መቃወስ ሳቢያ በማህበረሰብ ሆነ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ችግር አለ፡፡
ወ/ሮ ሽልማት እንግዳ አጠቃላይ ስልጠናው ሲሰጥ በስርዓተ ምግብ ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ መስራት አስፈላጊነቱን በመናገር ተመጣጣኝ ምግብ በገጠሩ ማህበረሰብ ከአካባቢያቸው ሳይርቁ የሚያገኙት እንደሆን ተናግረዋል፡፡የጓሮ እትክልት ማምረት በተለይ ሴቶች እና ህፃናት ይበልጡኑ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመሆን ሰጥቷል፡፡ሲስተር አልማዝ ዳርጌ ሰልጣኝ ሞዴሎች ለራሳቸውም ሆነ ለልጆቻቸው አስፈላጊ የሆነ ትኩረት በመስጠት በቤት ውስጥ እንክብካቤ በማድረግ በምግብ ራሳቸውን እንዱጠብቁ በማለት ተናግረዋል፡፡


