የድሬደዋ አስተዳደር የ2013ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ኢትዮጵያን እና ልብስ በሚል መሪ ሃሳብ የፊታችን ሀሙስ ነሃሴ 29/2013ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠዉን አቅጣጫ እንዲሁም የአስተዳደሩን ተጨባጭ የዝናብ ስርጭት ከግምት በማስገባት በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ 500ሺ የደንና የአግሮ ፎርሰትሪ ችግኞችን መትከል የሚያስችል ዝግጅቶች ተጠናቀው የችግኝ ስርጭት ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል፡
በዘንድሮው በአንድ ጀምበር 500ሺ ችግኞች ለመትከል ከታቀደው ዉስጥ 50 ፐርሰንት (250ሺ) በከተማ በሚገኙ 9 ቀበሌዎችና ተቋማት ሲሆን ቀሪዉ 50 ፐረሰንት (250ሺ) በገጠር በ4ቱም ክላስተሮች ተከላዉ የሚከናወን ሲሆን ከዚህም ውስጥ 70% (349,723ሺ) የደን ወይም የጥላ ዛፎች ሲሆኑ ቀሪዉ 26% (130,318) የፍራፍሬና አግሮፎርስትሪ እንዲሁም 4% (20ሺ) የዉበት ችግኞን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የአስተዳደሩ የአረንጓዴ አሻራ ቴክኒክ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
በዚሁ መሰረት በአስተዳደሩ 9 የከተማ ቀበሌዎች ውስጥ በተመረጡ የከተማ ቦታዎች 130,000 ችግኞች ፣ እንዲሁም በአራቱም ክላስተር በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች፡- ቢዮአዋሌ ክላስተር 71,095 ችግኝ ፣ ዋሂል ክላስተር 84,946 ጀልዴሳ ክላስተር 41,000 እና አሰሊሶ ክላስተር 53,000 ችግኞችን ለመትከል በተቀመጠው የድርጊት መርህ ግብር መሰረት ችግኞችን የማጓጓዝ ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል።


