የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 47ኛ መደበኛ ጉባኤን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል::

    የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት የምክር ቤቱ 2ኛ የስራ ዘመን 47ኛ መደበኛ ጉባኤ ከሀምሌ 27 እስከ ሀምሌ 28 ድረስ ይካሄዳል፡፡ በጉባኤውም የተለያዩ 11 አጀንዳዎች እንደሚቀርቡ ገልጸዋል፡፡ ከአጀንዳዎቹም መሀል የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤትን 2ኛ የስራ ዘመን 46ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለጉባኤን ማጽደቅ’የአስተዳደሩን አስፈጻሚ አካላት የ2013 የስራ አፈጻጸም እና የ2014 በጀት አመት እቅድ ገምግሞ ማጽደቅ’ የአስተዳደሩ ምክር ቤት ጽ/ቤትን ጨምሮ የአስተዳደሩን ተጠሪ አካላት የ2013 አፈጻጸም እና የ2014 በጀት አመት እቅድ ላይ ውይይት አድርጎ ማጽደቅ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የ2013 የበጀት አፈጻጸም እና የ2014 አጠቃላይ በጀት ማጽደቅ እንደሚገኙበት ጠቁመዋል፡፡ በመቀጠልም ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡