የኮቪድ-19 ቫይረስ በአስተዳደራችን የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ህብረተሰቡ የመከላከያ መንገዶቸን በአግባቡ እንዲተገብር ጥሪ ቀረበ፡፡

    የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ወ\ሮ ለምለም በዛብህ ዛሬ ሀምሌ 26/2013 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጪያ ህበረተሰባችን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ የኮሮና ቫይረስን እየተዘናጋ መሆኑን አብራርተዉ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ህብረተሰቡ የመከላከያ መንገዶችን በአግባቡ እንዲተገብር በማለት ጥሪ ቀረበ፡፡
    የኮቪድ-19 ቫይረስ በድሬ ደዋ መከሰቱ ከታወቀ ጊዜ ከመጋቢት 24/2012 ጀምሮ እስከ አሁን የ 38,530 ሰዎች የናሙና የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 5,295 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ። ከእነዚህም ዉስጥ 84 ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን እንዳጡ እና ከዚህ በላይ ጉዳት እንዳይደርስብን ህዝቡ የመከላከያ መንገዶቸን በአግባቡ እንዲተገብር በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
    በሀጉራችን አፍሪካ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 (3rd Wave) ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ በመሆናቸዉ ይህም ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ሁሉም ተረድቶ አስፈላጊዉን የመከላከያ መንገዶችን በአግባቡ መተግበር ይኖርበታል ብለዋል፡፡