ምክትል ከንቲባ ከድር ጁሀር ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ፣ ከብልፅግና ፓርቲ ፣ከፌደራል አቃቢ ህግ፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ፣ ከዘጠኙ የከተማ ቀበሌዎች ስራ አስፈፃሚዎች
ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርገዋል።
ምክትል ከንቲባው በከተማው የመሰረታዊ ፍላጎት እቃዎች ላይ ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ዋጋ በሚጨምሩ ፣ምርት በሚያሸሹና በሚያከማቹ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችና የሸማች ማህበራት ላይ የተጀመረው አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
እስከአሁን በተወሰደው እርምጃ ከ235 በላይ ሱቆችና መጋዘኖች መታሸጋቸውንና 6 ኤፍሲአር የጭነት መኪኖች ተይዘው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝም መገለፁን ንግድ ኢንዱሰትሪና ኢንቨሰትመንት ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ሐምሌ 28/2013 ዓ.ም.


