በድሬዳዋ አስተዳደር በአንድ ጀንበር 500 ሺ ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፅ፡፡

    በድሬዳዋ አስተዳደር በ3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአንድ ጀንበር 500 ሺ ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን በድሬዳዋ የአረጓዴ አሻራ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ የግብርናው ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የአረንጓዴ አሻራ በአንድ ጀንበር 500 ሺ ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጭያ ገለፁ፡፡
    የድሬደዋ አስተዳደር የ2013ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ኢትዮጵያን እናልብስ በሚል መሪ ሃሳብ በነገው እለት ሀሙስ ነሃሴ 29/2013ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠዉን አቅጣጫ እንዲሁም የአስተዳደሩን ተጨባጭ የዝናብ ስርጭት ከግምት በማስገባት በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ 500ሺ የደንና የአግሮ ፎርሰትሪ ችግኞችን መትከል የሚያስችል ዝግጅቶች መጠናቀቁን እና መላዉ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች በንቃት በመሳተፍ ለመረሃ ግብሩ ስኬት የድርሻዉን እንዲወጣ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡