የኢትዮጵያን እናልብስ አረንጓዴ አሻራ ዘመቻ መርሃ ግብር በድሬደዋ አስተዳደር ደረጃ ሁለት ሚልየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱ ተገለጸ::

    ሃሙስ ሃምሌ 28 በአንድ ጀምበር ግማሽ ሚልየን ችግኝ ለመትከል ቅደመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የድሬደዋ አስተዳደር ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ ተናግረዋል ፡፡
    እንደ ኃላፊው ገለጻ የችግኝ መትከል መርሃ ግብሩ ህጻናትን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች ፤ የሃገር ሽማገግሌዎች ፤ ዑጋዞች እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡ በቀጣይ ከድሬደዋ ባለፈ ለጎረቤት ሃገራት የሚሆን አንድ ቢሊየን ችግኝ ዝግጅት መደረጉን የቢሮ ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡
    በተመሳሳይ የድሬደዋ አስተዳደር ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኤሊያስ አልይ በአገራ አቀፍ ደረጃ ለሶስተኛ ጊዜ እተተገበረ ያለው የአረጓ አሻራ መርሃግብር ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እያሳየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
    እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከሃገር አቀፉ አጠቃላይ እቅድ የተቀዳ እቅድ በማዘጋጀት ሁለት ሚሊየን ችግኞችን ለመትከት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመረሃግብሩ ለመትከል ከታቀዱት ችግኞች ውስጥ በአመዛኙ አገር በቀል መሆናቸውን የገለጹጽ አቶ ኤያስ ፡፡ለችግኝ ተከላው የሚያስፈልጉ የጉርጓድ ቁፋሮ እንዲሁም የችግኝ ዝግጅት ተጠናወቋልም ብለዋል፡፡