ችግኝ መትከል በድሬደዋ ከውበት ባለፈ ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስና የአየር ንብረት ለውጥን ለማጣጣም ያለው አስተዋጾ የጎላ መሆኑን የድሬደዋ አስተዳደር የአካባቢ የደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ሃላፊ አቶ አብዱ መሃመድ ተናገሩ::

    የኢትዮጵያን እናልብስ አረንጓዴ አሻራ ዘመርሃግብር በድሬደዋ ደረጃ በነገው እለት በአንድ ጀንበር በከተማ 250ሺ እንዲሁም በገጠሩ የአስተዳደሩ ክፍል በተመሳሰይ 250 ሺ ጭግኞችን ለመትከል መታቀዱን አቶ አብዱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
    አክለውም በድሬደዋ ማህበረሰቡ ችግኝ የመትከል ልምድ እንዳለው የገለጹት ሃላፊው በቀጣይም ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ማጽደቅና ማሳደግ ባህሉ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
    ባለስልጣን መስሪያቤቱ ድሬደዋን አረንጓዴ ለማልበስ ብሎም ሌሎች በርካታ የአየር ንብረት ማጣጣሚያና ማስተሰሪያ ተግባራቶችን በላቀ ደረጃ በማቀድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል