ነገ ሃምሌ 28 2013 ዓም በድሬደዋ ደረጃ ሁለት ሚልየን ችግኝ ለመትከል የተያዘውን እቅድ አስመልክቶ በድሬደዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የልማት ተቋማት እቅድ ክትትል እና ግምገማ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዑመር አህመድ በሰጡት መግለጫ መርሃግብሩ እንደ ሌሎች ግዙፍ የልማት ስራዎች ሁሉ በከፍተኛ የደርጅት ቁርጠኛ አመራር እንዲመራ በየደረጃው ላሉ አመራሮች አቅጣጫ በመስጠት የተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በቀጠይም ይህ የኢትዮጵያን እናልብስ አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ሳይዳከም በከመፍተ የህብረተሰብ ተሳትፎ እየተፈጸመ እንዲዘልቅ ይደረጋል ያሉት አቶ ዑመር ህዝቡ ለቀጣዩ ትውልድ ጭምር ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጠውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በባለቤትነት ስሜት ተሳትፎ በማድረግ ለትግባራዊነቱ እንዲሰራ ጥሪ አቀቅርበዋል፡፡


