ለህብረተሰቡ ልማት እየሰራን ስላማችንን እናረጋግጣለን ሲሉ የቀበሌ 09 አመራሮች ገለፁ ::

    በቀበሌው የተሰሩ የልማት ሰራዎት የቀበሌው አመራር እና በባለድርሻ አካላት የመስክ ምልከታ የተደረገ ሲሆን በመስክ ምልከታው ላይ በመገኝት ንግግር ያደረጉት የቀበሌው ኮሙኒኬሽን እና የህብረተሰብ ተሣትፎ ልማት ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ አብዱልአዚዝ አህመድ እንደተናገሩት የዚህ አነስተኛ ደልዳይ ግንባታ የአካባቢው ነዋሪዎች በዝናብ ወቅትም ይሁን በሌላ ጊዜ የውሀ ፈሳሽ መውረጃና ተሸከርካሪም የማያሳልፈ በመሆኑ ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው ዘውትር የሚያነሱትን ጥያቄ መሆኑን አስታወሰው ለዚህም ሲባል በ2013 በጀት አመት ቀዳሚ በህብረተሰብ ተሣትፎ ልማት በቀበሌው ሊሰሩ ከታቀዱ የልማት ስራዎቸ ውስጥ በማካተት በአሁን ሰአት የድልድዩ ግንባታ አጠቃላይ አፈፃፀም 85 በ መቶ እንደደረሰ እና በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል የተሟላ አገልግሎት ይሰጣል በማለት ገልፀዋል፡፡
    የቀበሌ 09 ዋና ስራ አስፋፃሚ አቶ ሐሰን ኢጌ ይህ የነዋሪው የልማት ጥያቄ መቀረፍ እንዳስደሰታቸው በመግለፀ ከዚህ ድልድይ በተጨማሪም አንድ የውሀ ቦኖ ፕሮጀክት በቅርቡ እንደሚመረቅ እና በቀጣይም ለህብረተሰቡ ልማት እየሰራን የሀገራችንን ሰላም እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡
    በመጨረሻም በመስክ ምልከታው ላይ የተገኙ የቀበሌው አመራሮች እና የልማት ኮሚቴ አባላት በስራው ደስታቸውን በመግለፅ በቀጣይ ሊስተካከሉ ይገባል ያሉት ጉዳዮች አንስተዋል፡፡
    ድላድዩ 7.25 ሜትር ርዝማኔ እና 6.75 ስፋት እንዳለው ከቀበሌው የህብረተሰብ ተሣትፎ ልማት ማስተባበሪያ የግንባታ ቁጥጥር ባለሞያ ከሆኑት ከአቶ ከዲር አሊ ለማወቅ ተችሏል፡፡
    ምንጭ:- የቀበሌ 09 ኮሙኒኬሽን ማስተባበሪያ