ለሀገሬ እዘምታለው የትም፣ መቼም፣በምንም” በሚል መሪ ቃል ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲካሄድ አርፍዷል፡፡
በድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን አስተባባሪነት የስፖርት ቤተሰቡ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትን ጎን መሆኑን የሚገልፅ በከተማዋ ምድር ባቡር ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተካሄደበት ወቅት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድና ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሃር ” የአገር መከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ ያላቸውን አጋርነት ያረጋገጠ ነው ብለዋል”፡፡
የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽነን ኮሚሽነር አቶ ሻኪር አህመድ በበኩላቸው “እንደ ድሬዳዋ በስፖርት ዘርፍ ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ በተለያዩ ሁነቶች ተጠናክሩ እንደሚካሄድም ገልፀዋል ፡፡
የአገር መከላከያ ሠራዊትን በማወደስና ድጋፉን በማሳየት የስፖርት ቤተሰብ ደማቅ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የንቅናቄ መርሃ ግብር ላይ በድሬዳዋ ስፖርተኞች ፤ አሰልጣኞች ፤ ዳኞ ፤ ከአዋቂ እስከ ታዳጊ ወጣቶች ፤ ደጋፊዎች ፤ የስፖርት ባለሙያዎችና ሰራተኞች ፤ ቀበሌዎች ጨምሮ የስፖርት ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
በቀጣይም በድሬዳዋ አስተዳደር የስፖርት ንቅናቄ ኘሮግራም በደም ልገሳ ፤ በእግር ኳስ ውድድር ፤ በእግር ጉዞ ፤ በብስክሌት ፤ በጎዳ ሩጫ መሰል ዝግጅቶች እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል ፡፡


