ተቋሙ በ 2013 በጀት አመት ለ2 ሺ 404 ደንበኞች ከ 227 ሚሊዮን ብር በላይ የብድር ስርጭት ማድረጉንም ነው ያስታወቀው ፡፡
በ 1994 ዓ.ም የተቋቋመው የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም ባለፉት አመታት በተለይም በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማም ሆነ በገጠር ለሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ፣ እንዲሁም ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ፡፡ ተቋሙ በ 2013 በጀት አመትም ለ 2 ሺህ 305 ደንበኞች 200 ሚሊዮን ብር በብድር መልክ ለማሰራጨት አቅዶ በበጀት አመቱ ለ 2 ሺህ 404 ደንበኞች ከ227 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር በማሰራጨት ከእቅድ በላይ መሰራቱን የድሬ ብድርና ተቋም ዋና ስራ-አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተሾመ አበበ ተናግረዋል ፡፡
አቶ ተሾመ አክለውም የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ባለው የጋራ ግንኙነት አማካኝነት የከተማዋን ነዋሪዎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደተቻለና በቀጣይም አስተዳደሩንም ሆነ የከተማዋን ነዋሪዎች በኢኮኖሚ እየደገፈና እያገዘ ሊሰራ የሚችል ተቋም መሆኑን ተናግረው በቀጣይ በ 2014 በጀት አመትም ለ 3 ሺህ 705 ደንበኞች 480 ሚሊዮን ብር ለደንበኞች ብድር ለማሰራጨት በእቅድ ደረጃ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን ነው አቶ ተሾመ የተናገሩት::
ተቋሙ የ 2013 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም የ 2014 በጀት እቅድ ላይም ውይይት አካሂዷል፡፡
የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም የድሬዳዋን ነዋሪዎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉ ተገለፀ፡፡


