“ኢትዮጵያን ለማዳን የቱንም ርቀት እንጓዛለን፤ የቱንም መስዋዕት እንከፍላለን!” በሚል መሪ ቃል ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ የድጋፍ እግር ጉዞ በድሬዳዋ::

    ማክሰኞ ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ መነሻውን ከፋይናንስ በማድረግ፣ በመስቀለኛ፣ በማደያ ወደ አውራጎዳና አድርጎ መዳረሻውን ለገሀር አደባባይ ያደረገ የድጋፍ እግር ጉዞ ይደረጋል::
    በእለቱ በለገሐር አደባባይ:-
    🇪🇹 ኢትዮጵያን የማዳን ድምፃችንን በአንድነት እናሰማለን፣
    🇪🇹 የሰራዊቱ ደጀን እንደሆንን ቃል እየገባን “ደማችንን ለመከላከያ ሠራዊታችን እንለግሳለን”፣
    እንዲሁም ኢትዮጵያዊነትን በሚያቀነቅኑ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ሰራዊቱን እናጀግናለን::
    መላው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ኑ በአንድነት ሆነን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከፍ እናድርግ!