የድሬዳዋ አስተዳደር አራቱ የገጠር ክላስተር ስር የሚገኙ 38 የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በአይነትን እና በገንዘብ ያዋጡት በአይነትን 25 በሬዎች፣ 85 ፍየሎች እና 2 ግመሎች እንዲሁም በገንዘብ በድምሩ 3 ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አበረከቱ፡፡
በድጋፍ ርክክቡ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ኡስማን አህመድ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት የድሬዳዋ ገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች ሀገር ለማዳን እየተደረገ ባለዉ ዘመቻ ላይ አሳን ከውሃ መለየት እንደማይቻል ሁሉ ልክ እንደ መላዉ የሀገራችን ብሄር፣ ብሄረረሰቦች እና ህዝቦች ሁሉ የድሬ ዳዋ አስተዳደር የገጠር እና የከተማ ቀበሌ ነዋሪዎችም ከብሄራዊ አንድነታቸው መነጠል እንደማይቻል በተግባር ያረጋገጡበት መሆኑን አብራተዋል፡፡
በስነስርዓቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በበኩላቸዉ መላዉ የአስተዳደራችን ነዋሪዎች ሀገር ለማዳን እየተደረገ ባለዉ ዘመቻ ላይ በቀዳሚነት በሁሉም ዘርፍ የተለያዩ ድጋፎችን እያበረከተ እንደሚገኝ እና ይህ መሰል ድጋፍ ለሁለተኛ ጊዜ ማበረከቱን ገልፀው በቀጣይም ይህን መሰል ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በድጋፍ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀረር እና የድሬዳዋ የላይዘን ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ኮሮኔል ዮናስ ሮባ በብኩላቸዉ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትችን አገራችንን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ የአሸባሪው የህወኅት ቡድንና ተላላኪዎቹን በሚገባ እየድመሰሰ እንደሚገኝ አብራርተዉ ህዝባችን እና የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ሀገራችንን ከውስጥና ከውጪ ጠላቶች በጋራ ድል ማድረጋችን የማይቀር ነዉ ብለዋል።


