የ01፣02 እና 03 ቀበሌ ነዋሪዎች በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል
በውይይቱ ወቅታዊ አገራዊ ነባራዊ ሁኔታን የሚመለከት ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተካሂዷል:-
ህዝቡ አካባቢውን ካለመዘናጋት በንቃት በመጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ መስራት ይገባል::
**በህልውናችን ላይ እየተቃጣ ያለ ዘመቻ በመሆኑ ዜጎች ከመንግስት ጋር በመሆን መመከት አለበት።
መከላከያን በገንዘብም በሃይልም በቁስሳቁስም መደገፍ አለብን።
በተለያዩ መንገዶች የውጭ አካላት እጃቸውን እንዲሰበስቡ የሚያመላክት ድምፅ ማሰማት አለብን
ወጣቱ በያለበት በመደራጀት አካባቢውን በንቃት መጠበቅ እንደሚገባው ሃሳብ ተንፀባርቋል።
መንግስት ዜጎች ያለውን እውነታ በአግባቡ እንዲረዱ ተከታታይነት ያለው መረጃ ማድረስ እንዳለበት ሃሳብ ተነስቷል።
በአጠቃላይ ወቅቱ አገራቸወንን እና ህዝቦቿን አንገት ለማስደፋትና ለማፈራረስ የውስጥ ጠላት ከውጭ ሃይሎች ጋር በማበር አየተንቀሳቀሱ ያሉበት ጊዜ እንደመሆኑ ለህልውና ዘመቻው ወደግንባር በመዝመት እንዲሁም ሁለም ዜጋ በየተሰማራበት ዘርፍ ውጤታማ በመሆን ለሃገሩ ያለውን ፍቅር በተግባር ማስመስከር እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።


