””ለወገኖቻችን የምናደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል”’

    አቶ ሱልጣን አልዬ
    የድሬደዋ አስተዳደር ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ
    የቢሮ ሃላፊው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ጁንታው እየፈፀመ ያለው ወረራና የሽብር ተግባር በዲሞክራሲያዊ መንገድ በህዝብ የተመረጠ መንግስትን ከውጭ ሃይሎች ጋር በመተባበር ለማፍረስ እንዲሁም ኢትዮጵያን ለመበታተን ያለመ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሃገሩን ሉአላዊነት ለማስከበር በአንድነትና በመተባበር በጋራ የሚቆምበት ጊዜ መሆኑን አስረድተዋል።
    አቶ ሱልጣን አክለውም በድሬደዋ አስተዳደር በአማራና በአፋር አሸባሪው ህውሃት ባደረገው ወረራ ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ወገኖች በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ እየተደረገ እንደሚ ተናግረዋል።
    በሰሜኑ የሃገራችን ከወፍል እና በአፋር ክልል ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ለተከሰተው ድረቅ በገንዘብም በአይነትም ድጋፍ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ የድጋፍ የማሰባሰቡ ስራ የገቢና ሎጂስቲክ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰፊ ስራ እተከናወነ እንደሚገኝ አቶ ሱልጣን አብራርተዋል
    ህዝቡ ለሚጠየቀው ድጋፍ ሁሉ በሙሉ ፍላጎት እያበረከተ እነወደሚገኝ ወደፊትም የተጋረጠብንን ችግር ድል እስከምናደርግ ድረስ ይሀወንኑ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ ሱልጣን ጥሪ አቅርበዋል።
    ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ማንኛውንም ድጋፍ ለማበርከት ከፈለገ በየቀበሌው የተዘጋጀ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ማዕከል መዘጋጀቱን ሃላፊው አስረድተዋል።