በድሬዳዋ አስተዳደር የከተማዋን ጽዳትና ውበት ለማስጠበቅ በአስተዳደሩ ከንቲባና ም/ከንቲባ የሚመራና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ነዋሪውን በማሳተፍ መከናወን የጀመረው የጽዳት ዘመቻ፤ ዛሬም በ06 ቀበሌ ከቀፊራ – በ5ኛ – ለሀገሬ አዋሳኝ መንገድ፤ እንዲሁም በመልካ ጀብዱ ኢንደስትሪያል ፓርክ በተከናወነው የችግኝ እንክብካቤ ቀጥሏል።
በ06 ቀበሌ በተከናወነው የፅዳት ዘመቻ ማብቂያ ወቅት በአስተዳደሩ ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንዳሉት፤ የከተማዋን ጽዳትና ውበት ለማስጠበቅ እየተከናወነ የሚገኘው የጽዳት ስራ በአግባቡ ከግብ እንዲደርስ፤ የቀበሌው ነዋሪዎች የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በአጭር ጊዜ መስተካከል እንደሚገባው አሳስበዋል።
በዘመቻው የተሳተፉ ነዋሪዎች በበበኩላቸው አካባቢያቸውን ማጽዳት የመኖሪያ አካባቢን ውበት ከመጠበቅ ባሻገር ጤንነታቸውን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ ዘወትር ይህን ተግባር ለመከወን ዘመቻው መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።


