የቅዳሜ እሁድ ገበያ ተጧጡፎ ቀጥሏል በድሮ ማዘጋጃ ቤት ፊትለፊት የከተማው ነዋሪ መሰረታዊ ፉላጎቱን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያሟላበት የቅዳሜና እሁድ ገበያ በሁለተኛ ዙሩ በርካታ የከተማ ሽማቾችን ስያስተናግድ ውሉዋል ።

    በቅዳሜና እሁድ ገበያው ተዘዋውረን እንደተመለከትነው ህብረተሰቡ ለእለተ ዕለት የቤት ውስጥ ፍጆታ የሚጠቀምባቸው የሀገር ውስጥ የውጪ ምርቶች የሆኑ የምግብ፣መጠጥ፣የንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶች፣የእንዱስትሪ ውጤቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ቀርበው ሲሽጡ ውለዋል ።
    በገበያ ስፍራው ያገኘናቸው ሽማቾች በሰጡን አስተያየት በቅዳሜና እሁድ ገበያ የቀረቡ ምርቶች ጥራት ያላቸው ምርቶች መሆናቸውና ከዋጋ አንጻሪም ከፍተኛ ቅናሽ ያለው በመሆኑ ህብረተሰቡን በይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ገበያው በአንድ ቦታ ብቻ ሳይወሰን በሌሎች አከባቢዎችም መስፋፋት እንዳለበት ጠቁመዋል ።
    በድሬዳዋ አስተዳደር የ ን.ኢ.እንቬስትመንት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዲ ሙክታር ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የቅዳሜና እሁድ ገበያ ከጅምሩ በህብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን ገልጽው በየሳምንቱ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በቅዳሜና እሁድ ቀናት የሚካሄደው ገበያ ህብረተሰቡ የኑሮ ውድነትን በመቋቋም ህይወቱን በአግባቡ መምራት እንዲችል ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በቀጣይ በለገሃሬ አስታጥቄ ሜዳ፣በሰኢዶ ጉሊት ፣በአሽዋ አሽዋ ገበያ እና በ 04 ቀበሌ አከባቢ የቅዳሜና እሁድ ገበያ በመክፈት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አቶ አብዲ አብራርተዋል
    በቅዳሜና እሁድ ገበያ መንግስት የኑሮ ውድነትን ለመከላከል ከቀየሳቸው ስልቶች መካከል አንዱ ሲሆን በዚህ የ ግብይት ህደት ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ህብረተሰቡን ከክሳራ ለማዳን የተቻለበት ከጅምሩ ጥሩ ውጤት ያስገኘ ተግባር በመሆኑ የቅዳሜና እሁድ ገበያን የማስፋት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አብዲ ገልጸዋል።
    ህብረተሰቡ ቅዳሜ እና እሁድ በገበያ ስፍራው በመገኘት በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበለትን ምርቶች በመሽመት የእዲሉ ተጠቃሚ እንዲሆን ሃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል