በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12:00 ሰአት ጀምሮ በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፅዳት ዘመቻ የተካሄደ ሲሆን በዚሁም የፅዳት ዘመቻ ላይም የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና የኢንዱስትሪ ፓርኩ ሰራተኞችን አመራሮች በተገኙበት የፅዳት ዘመቻው ተካሄዷል።
የፅዳት ዘመቻው በየሳምንቱ መካሄዱ በነዋሪው ህብረተሰብ ላይ ጥሩ የሆነ መነሳሳትን ከመፍጠሩም ባለፈ በቀጣይም የፅዳት ዘመቻውን ህዝባዊ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ ተናግረው ከ 8 ተኛው ዙር በኋላ የፅዳት ዘመቻውን ህዝባዊ ከማድረግ አኳያ በአስተዳደሩ ውስጥ ያሉ ተቋማት ፣ በየቀበሌ ያሉ አመራሮችና ነዋሪዎች በመናበብና በየአካባቢው በመሆን ይሄን የፅዳት ዘመቻ በቋሚነት እንዲይዙት እንደሚደረግ አቶ ሀርቢ ቡህ በእለቱ ተናግረዋል ።
በዚህ በክረምት ወቅት ከአስተዳደሩ ጋር በጋራ በመሆን በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ 120 የሚሆኑ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 70 ሺህ የሚሆኑ ችግኞች መተከላቸውን የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ-አስኪያጅ የሆኑት አቶ ካሚል ኢብራሂም ተናግረው እነዚህ የተተከሉትን ችግኞች ከመከባከብ አኳያ አሁን ላይ የተጀመሩት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አቶ ካሚል በፅዳት ዘመቻው ላይ ተናግረዋል ።


