በቀበሌው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ሽኝት ስነስረዓት ተካሂዷል።
በስነስረአቱ ላይ በድሬደዋ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሃላፊ ተወካይ አቶ ገበየሁ ወጋየሁ የህዳሴ ግድባችን በህዝብ ተሳትፎ መገንባቱን እንደቀጠለ አስታውሰው ህዝቡ ለግድቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።በድሬደዋ አስተዳደር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለት ሚሊየን ብር ማሰብሰቡን ተናገረዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በአስተዳደራችን በየቀበሌው መዞሩ የህዝብ ንቅናቄን እየፈጠረ እንዲሁም ተጨማሪ ገቢ እንዲሰበሰብ እያስቻለ መሆኑን አቶ ገበየሁ ገልፀዋል።
የ04 ቀበሌ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሃምዲ መሃመድ በቀበሌው ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ሁለት መቶ ሺህ ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ ስድስት መቶ ሺ ብር ገቢ ለመሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ቀጣይ ተረካቢ ቀበሌ 05 ሆኗል።


