የድሬዳዋ የእስልምና እምነት መሪዎችና፤ የመስጂድ ኢማሞች በወቅቱ ሀገራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።

    በምክክሩ የአሸባሪው ህወኀት ቀዳሚ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙትን፤ የእምነት ተቋማትና አካባቢያችንን ከጥፋት ለመከላከል፤ ሁሉም አባቶችና መምህራን እውነተኛ መረጃ ላይ በመመስረት፤ የእምነቱ ተከታዮችን ማስተማርና ማረጋጋት ይገባል ተብሏል።
    ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር እና በምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ የሆኑት የፓርቲያችን ጽ/ቤት ኀላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በመሩት መድረክ ህዝብንና ሀገርን ከጥፋት ሀይሎች እየጠበቀ የሚገኘውን መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ዘርፍ መደገፍና ለሀገር ሰላም መፀለይ፤ በእምነቱ አባቶች ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ኀላፊነት እንደሆነ አፅንኦት ተሰጥቶበታል።
    አካባቢያችንን እንጠብቅ❗
    ወደ ግንባር እንዝመት❗
    ሠራዊታችንን እንደግፍ❗
    ምንጭ፡- Dire_PP