ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ዝግጅት
የድሬዳዋ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሰራተኞች ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ዝግጅት አከናወኑ፡፡
በስንቅ ዝግጅት ስነ ስርዓቱ ላይ ድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ክድር ጁሀር እና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተገኝተዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ክድር ጁሀር የስንቅ ዝግጅት ስነ-ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት ይህ በጎ ተግባር በማበረታታትና በመደገፋቸው እንዲሁም ሰራተኞቹ ይህንን በማድረጋቸው በአስተዳደሩ ስም አመስግነዋል፡፡
ከንቲባ ከድር ከዚህም ጋር በማያያዝ በቀጣይም ይህንን በጎ ተግባር እንዲያስቀጥሉ እና ሌሎች መስሪያ ቤቶችም ይህንን በጎ አላማ በአርአያነት በመውሰድ እንዲተገብሩት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ለድሬዳዋ ት/ቢሮ የሳኒታይዘርና ፈሳሽ ሳሙ ለአስተማሪዎችና ለተማሪዎች መገልገያ የሚሆን ድጋፍ አድርገዋል፡፡


