ኮቪድ 19 በመከላከል የመማር ማስተማር ህደቱን ለማስቀጠል የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

    ኮቪድ 19 በመከላከል የመማር ማስተማር ህደቱን ለማስቀጠል የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ለትምህርት ተቋማት አስፈላጊውን ግብዓት ለማሟላት ትምህርት ቢሮ ባቀረበው ጥሪ መሠረት መንግስታዊና መ/ያልሆኑ ድርጅቶች የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።
    የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ግምታቸው 20,000 (ሃያ ሺህ ብር ) የሁኑ የተለያዩ የትምህርት መርጃ እና ንጽህና መጠበቂያ ግብአቶችን በመግዛት ለትምህርት ቢሮ አስረክበዋል።
    የትምህርት መርጃ እና የንጽህና መጠበቂያ ግብአኣቶቹ በትምህርት ተቋማት የኮቪድ 19 በሽታ ስርጭትን በመከላከል የመማር ማስተማር ሂደት የማስቀጠል ስራ ለትምህርት ቢሮ ብቻ የሚተው ጉዳይ ሳይሆን የሁሉም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ቢሮው ኃላፊነቱን ለመወጣት ከ ማኔጅመንት አባላት ጋር በመምከር ድጋፍ ማድረጉን የመንግስ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሂስቅያስ ታፈሰ በርክክብ ስነ ስርዓት ወቅት ገልጸዋል።
    የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ በበኩላቸው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የኮሮና ወረርሽን ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ህብረተሰቡ ለበሽታው እንዳይጋለጥ ስርጭቱን ለመከላከል በሚደረገው የህብረተሰብ ንቅናቄ ስራዎችን በመስራት ከፍተኛ ድጋፍ ከማድረጉም ባሻገር የትምህርት መርጃ ግብአቶችን በመግዛት አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማድረግ በትምህርት መርጃ ግብአት እጦት ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዳይሆን ለሚናደርገው እንቅስቃሴ ድጋፍ እያደረገልን ስለሆነ ከልብ እናመስግናለን ብለዋል።
    ድጋፉን በ መንግስ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ ላይ ያሉ አመራሮች ለወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ያስረከቡ ስሆን ባለ 100 እና 50 ሉክ ደብተር፣እስክሪብቶና እርሳስ፣ሳኒታይዘር እና ማስክ ከ ድጋፎቹ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው