የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ውይይት አካሄዱ።
የአስተዳደሩ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱ በአስተዳደሩ የሚገኙ አመራሮች የተሰጣቸውን ስምሪት በአግባቡ በመወጣት የፀጥታና የሰላም እንዲሁም የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል በሚሳካበት ሁኔታዎች ዙሪያ መክረዋል።
ከመደበኛ ጦርነቱ በተጨማሪም የኢኮኖሚ ጦርነቱን ለመመከት መቀናጀት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በመጨረሻም የተለያዩ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የአስተዳደሩ አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስተራችን ጎን እንቆማለን፣ የምዕራባዊያን ጫና አንቀበልም በማለት በ#NoMore #በቃ ዘመቻ ስብሰባውን ተጠናቋል፡፡


