የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ለተቋሙ ሰራተኞችና ለተጠሪ ተቋማት የሪብራንዲንግ ፅንሰ ሀሳብ አስፈላጊነትና አተገባበር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል ።

    የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ለተቋሙ ሰራተኞችና ለተጠሪ ተቋማት የሪብራንዲንግ ፅንሰ ሀሳብ አስፈላጊነትና አተገባበር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል ።
    የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት እንደ ሀገራችን ብሎም በአስተዳደራችን ከተጀመረው አዲስ ምእራፍ ጉዞ ጋር ተያይዞ የተገኘውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በአዲስ ቅኝት የተቀረፀውን የሪብራንዲንግ ፅንሰ ሀሳብ በውስጡ የያዘውን ዋና ዋና ማእቀፍና የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማገናዘብና ከሞላ ጎደል በተገልጋዮች ዘንድ በአሉታዊው ገፅታው የሚነሳውን በፅህፈት ቤት ወደ አዎንታዊ ገፅታ በመቀየር እንዲሁም በጥሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ላይ ያሉትን ዳይሬክቶሬቶች በማበረታታትና ውጤቱንም ተቋማዊ አድርጎ ለማስቀጠል ይቻል ዘንድ የሪብራንዲንግ ፅንሰ ሀሳብ አስፈላጊነትና አተገባበር ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ መሰረታዊ ሀሳብ በመሆኑ ምክንያት ለተቋሙ ሰራተኞች ብሎም ለተጠሪ ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ።
    በዚሁም መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ገበየው ጥላሁን መንግስት የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች እንዲሁም የተለያዩ ተልእኮዎችን በብቃትና በውጤታማነት መወጣት የሚችሉት ፐብሊክ ሰርቫንቱ የመንግስትን የልማት የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ በተሟላ መልኩ ተገንዝቦና የራሱ አድርጎ እለት ተእለት በብቃት መፈፀም የሚችሉ ፐብሊክ ሰርቫንቶች ሲኖሩ ብቻ መሆኑን አቶ ገበየው ጥላሁን ተናግረዋል ።
    ሀላፊው አክለውም ሀገራችን አሁን ላይ ከገባችበት ችግር ትወጣ ዘንድ የበኩላችንን ሚና ከመወጣት ባለፈ ነዋሪውን ህብረተሰብ በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል እንደሚገባም ነው አቶ ገበየው በእለቱ የተናገሩት ።